በሕግ አግባብ የተያዘዉ የቤተክርስቲያን ቤት በዶዘር ፈረሰ ሰሚ ያጣዉ የቤተክርስቲያን ቤት በመንግስት በኩል በሐይልና በጉልበት የፍርድ ቤትን እግድ ወደ ጎን በመተው እያፈረሱት ይገኛልሚያዚያ 12/2016 ዓ.ም(ፍ.እ.ሚ./አዲስ አበባ)

በሕግ አግባብ የተያዘዉ የቤተክርስቲያን ቤት በዶዘር ፈረሰ ሰሚ ያጣዉ የቤተክርስቲያን ቤት በመንግስት በኩል በሐይልና በጉልበት የፍርድ ቤትን እግድ ወደ ጎን በመተው እያፈረሱት ይገኛል

ሚያዚያ 12/2016 ዓ.ም(ፍ.እ.ሚ./አዲስ አበባ)

በምሥራቅ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት በሐረር ከተማ የሚገኘው ጥንታዊው እንቁላል ቤት ወይም የቀድሞ እስታስቲክ ቢሮ የነበረበት እና መንግስት እስከ 2016 ዓ.ም ድረስ የግብር አበል ለቤተክርስቲያኒቱ ግብር እየከፈለበት የነበረው የቤተክርስቲያናችን ቤት በሐረሪ ክልል መንግስት በኩል የማፍረስ ሥራ እየተከናወነበት ይገኛል። 

ከዚህ በፊት ቤተክርስቲያኒቱ በተደጋጋሚ በመንግሥት በጊዜያዊም ይሁን ባልታወቁ ሁኔታዎ የተወሰዱና መሰል ጉዳዮች ጨምሮ ቤቶቹ ለቤተክርስቲያን እንዲመለስላት ከ25 ዓመታት በላይ ቤተክርስቲያን ጥያቄ እያቀረበች የነበረ መሆኑ ይታወቃል ከእነዚህም ቤቶች መካከል አንደኛውና በከተማው ዋና የገበያ ማዕከል አካባቢ የሚገኘዉ ንብረትነቱ የቤተክርስቲያኒቱ የሆነዉ ይዞታ ከ15 ቀን በፊት በመንግሥት ይፈለጋል ለብልጽግና ጽ/ቤት መስሪያ በማለት በዶዘር ቤቱኑን የማፍረስ ሥራ እየተካሄደ ባለበት ወቅት የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ መልአከ ገነት ቀሲስ ንጋቱ ደሳለኝ ከክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጀምሮ ከሚመለከታቸዉ አካላት በመነጋገር ወዲያዉኑ የማፍራስ ሥራዉ እንዲቆም ተደርጓል በማስቀጠልም በበነጋታው ጉዳዩ በፍርድ ቤት በኩል እልባት እንዲያገኝና የፍርድ ቤት እግድ ወጥቶበት ለሚያዚያ 15/2016 ዓ.ም አፍራሽ የመንግስት አካላት መልስ እንዲሰጡበት ተወስኖ እያለ 
በዛሬዉ ዕለት ሚያዚያ 12/2016 ዓ.ም ከጠዋት ጀምሮ የማፍራስ ሥራዉ ተጠናቆ ፍራሹን በዶዘርና በተሽከርካሪ መኪኖች እያስወገዱ እያለ የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ መልአከ ገነት ቀሲስ ንጋቱ ደሳለኝ በቦታዉ ተገኝተዉ የማፍረስ ሥራው እንዲቆምና መፍትሔ እንዲሰጣቸዉ ወደ ክልሉ የመንግስት አካላት ጋር ስልክ በተደጋጋሚ ቢደዉሉም ምንም አይነት የማፍረስ ተግባሩን የሚያስቆም አካል ባለመኖሩ ሥራ አስኪያጁ ሰሚ በማጣታቸውና በበቦታዉ የሚገኙትን ሠራተኞችንና አሠሪዎችን የፍርድ ቤት እገዳዉን ወረቀት ቢያሳዩአቸና ቢያናግሩም እኛ የምናዉቀዉ ጉዳይ የለንም ታዘን ነዉ በማለት ለሥራ አስኪያጁ ምላሽ ሰጥዉ የቤተክርስቲያኒቷን ጥንታዊ ቤት የማፍረስ ሥራቸውን ቀጥለዋል ክቡር የሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅም ሰሚ በማጣታቸዉና መፍትሔ ሰጪ አካል ባለመኖሩ ሲያዝኑ ተመልክተናል።

ክቡራትና ክቡራን ዉድ የቤተክርስቲያን ልጆች ሁላችሁም በያላችሁበት የቤተክርስቲያንን ድምፅ እንድታዳምጡና ያለመለያየት እንደ አንድ ልብ መካሪ እንደ አንድ ቃል ተናገሪ በመሆን የበኩላችሁን እንድትወጡ ቅድስት ቤተክርስቲያን ዛሬም ጥሪዋን ታቀርባለች።

  "👉በህግ አግባብ የተያዙ የቤተክርስቲያን ጥያቄ በአግባቡ ይመለሱ
  👉በህገ መንግስቱ የተሰጠው የሃይማኖት ነፃነት ሙሉ በሙሉ ይከበር
  👉የቤተክርስቲያን ይዞታ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ይከበር 
  👉የሃይማኖት አባቶች ስለቤተክርስቲያን የሚያቀርቡት ህጋዊ ጥያቄ በህግ አግባብ ሊደመጥና ሊመለስ ይገባል
👉የህግ የበላይነት ማክበር የሁሉም ድርሻ ኃላፊነት ነዉ"

© ምስራቅ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት

Comments

Popular posts from this blog

Ethiopia celebrates 46th Anniversary of Karamara Victory

Kissinger and Lord Macaulay on Ethiopia

Waxay yiraahdeen "Xusuuso 1977".