Posts

Showing posts from December, 2024

Waxay yiraahdeen "Xusuuso 1977".

Image
Waxay yiraahdeen "Xusuuso 1977".  ===================  Hogaamiyihii kibirka badnaa ee Soomaaliya, taliskii Ziadbare, waxa uu xukunka qabtay 1969-kii ka dib markii uu afgambiyay dawladdii markaas talada dalka haysay.  1977-kii ayay duullaan ku qaadeen Itoobiya, 1978-kii, qiyaastii saddex meelood meel meel askartii iyo 50% diyaaradihii loo soo diray inay weeraraan ayaa ka baxay Itoobiya.  Jabkii ka dib, Soomaalidu waxay billaabeen inay ciidan isku amarto. Intaa ka dib, Soomaaliya way kala tagtay oo waxay noqotay dawlad la’aan.  Tani waa sheekada aan ognahay. Sheekada dunidu ogtahay waxay tahay in Ziadbare fartiisu taabatay Itoobiya. Fartan #Ziadbare waxay cudur daar u tahay in loo soo jeesto Soomaaliya ka dib dhadhamin jabka.  Maanta waxaan ogaaday in Soomaalida aduunka oo dhan ay soo galiyeen ra'iisul wasaare Dr. Abiy Ahmed boggiisa FB ee ay ku leeyihiin "Xusuuso 1977".  sxb maxaa kale oo ay Somaliya qabsatay 1977, marka laga reebo qabsas...

አሰብ የማን ናት?

Image
s    “አሰብ የማን ናት?”ን በጨረፍታ አሰብ የማን ናት?”ን በጨረፍታ በ260 ገጾች  ተቀንብቦ የተጻፈው የዶ/ር ያዕቆብ ኃ/ማርያም ‹‹አሰብ የማን ናት?›› ዶ/ሩን የሚያስመሰግን፣ ኢትዮጵያውያንን የሚያነቃቃ ነው፡፡ መጽሃፉን እያነበብኩ እያለሁ ይሰማኝ የነበረው ስሜት በመዳን ላይ ያለ ቁስል ዳርዳሩን ሲያኩት የሚሰጠውን ዓይነት ስሜት ነበር፡፡ (የምታውቁት ካላችሁ) የመጽሃፉ መግቢያ፣ የመጀመሪያው አንቀጽ ‹‹ኢትዮጵያውያን በተለያዩ የታሪክ ወቅቶች በአገር ውስጥ ብቅ ያሉ አምባገነን መሪዎች የጫኑባቸውን በደሎች ሰው ሰራሽም ሆኑ ተፈጥሮ የወለደቻቸውን ችግሮች በትዕግስት ያስተናገዱ ሲሆን፤ ኢትዮጵያውያን በትዕግሰት የማይመለከቱት ነገር ቢኖር የድንበር መደፈርን ነው ማለት ይቻላል፡፡›› ይላል፡፡ የመጽሃፉ ዓላማ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ አሰብ የኢትዮጵያ መሆኗን አውቆ የባሕር በራችንን ማስመለስ ብሔራዊ ግዴታችን እንደሆነ ለማስታወስ መጣር መሆኑም በመግቢያው ላይ ተገልጧል፡፡ ምዕራፍ አንድ፤ የባሕር በርና ፋይዳው ኢትዮጵያ የምትከራያቸው የጎረቤት አገር ወደቦች ርቀታቸው ከአዲስ አበባ፣ ከ910 ኪ.ሜ. (ጅቡቲ) እስከ 1804 ኪ.ሜ. (ሞምባሳ) ይደርሳሉ፡፡ የአሰብ ወደብን ብንጠቀም ግን 640 ኪ.ሜ. ብቻ (ከኢትዮጵያ የአሁኑ ክልል ደግሞ 60 ኪ.ሜ. /የእግር መንገድ ርቀት/) ወይም ከጅቡቲ አንፃር የአንድ ቀን የመኪና ጉዞ መቅረብ ትችላለች፡፡ ወደብ የሌላቸው ድሃ ሃገራት የውጭ ንግዳቸው ከ33 እሰከ 43 በመቶ ሊቀንስ ይችላል፡፡ ከዚህም በላይ ኢትዮጵያ ለወደብ ኪራይ በየቀኑ ከ3 ሚሊዮን ዶላር (ልብ በሉ ብር አላልኩም በየቀኑ 3 ሚሊዮን ዶላር) ታወጣለች፡፡ ከዚህም በከፋ መንገድ በኢኮኖሚ ዕድገት አንድ ወደብ ያለው አገር በ24 ዓመት ኢኮኖሚው እጥፍ ማደ...

በሕግ አግባብ የተያዘዉ የቤተክርስቲያን ቤት በዶዘር ፈረሰ ሰሚ ያጣዉ የቤተክርስቲያን ቤት በመንግስት በኩል በሐይልና በጉልበት የፍርድ ቤትን እግድ ወደ ጎን በመተው እያፈረሱት ይገኛልሚያዚያ 12/2016 ዓ.ም(ፍ.እ.ሚ./አዲስ አበባ)

Image
በሕግ አግባብ የተያዘዉ የቤተክርስቲያን ቤት በዶዘር ፈረሰ ሰሚ ያጣዉ የቤተክርስቲያን ቤት በመንግስት በኩል በሐይልና በጉልበት የፍርድ ቤትን እግድ ወደ ጎን በመተው እያፈረሱት ይገኛል ሚያዚያ 12/2016 ዓ.ም(ፍ.እ.ሚ./አዲስ አበባ) በምሥራቅ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት በሐረር ከተማ የሚገኘው ጥንታዊው እንቁላል ቤት ወይም የቀድሞ እስታስቲክ ቢሮ የነበረበት እና መንግስት እስከ 2016 ዓ.ም ድረስ የግብር አበል ለቤተክርስቲያኒቱ ግብር እየከፈለበት የነበረው የቤተክርስቲያናችን ቤት በሐረሪ ክልል መንግስት በኩል የማፍረስ ሥራ እየተከናወነበት ይገኛል።  ከዚህ በፊት ቤተክርስቲያኒቱ በተደጋጋሚ በመንግሥት በጊዜያዊም ይሁን ባልታወቁ ሁኔታዎ የተወሰዱና መሰል ጉዳዮች ጨምሮ ቤቶቹ ለቤተክርስቲያን እንዲመለስላት ከ25 ዓመታት በላይ ቤተክርስቲያን ጥያቄ እያቀረበች የነበረ መሆኑ ይታወቃል ከእነዚህም ቤቶች መካከል አንደኛውና በከተማው ዋና የገበያ ማዕከል አካባቢ የሚገኘዉ ንብረትነቱ የቤተክርስቲያኒቱ የሆነዉ ይዞታ ከ15 ቀን በፊት በመንግሥት ይፈለጋል ለብልጽግና ጽ/ቤት መስሪያ በማለት በዶዘር ቤቱኑን የማፍረስ ሥራ እየተካሄደ ባለበት ወቅት የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ መልአከ ገነት ቀሲስ ንጋቱ ደሳለኝ ከክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጀምሮ ከሚመለከታቸዉ አካላት በመነጋገር ወዲያዉኑ የማፍራስ ሥራዉ እንዲቆም ተደርጓል በማስቀጠልም በበነጋታው ጉዳዩ በፍርድ ቤት በኩል እልባት እንዲያገኝና የፍርድ ቤት እግድ ወጥቶበት ለሚያዚያ 15/2016 ዓ.ም አፍራሽ የመንግስት አካላት መልስ እንዲሰጡበት ተወስኖ እያለ  በዛሬዉ ዕለት ሚያዚያ 12/2016 ዓ.ም ከጠዋት ጀምሮ የማፍራስ ሥራዉ ተጠናቆ ፍራሹን በዶዘርና በተሽከርካሪ መኪኖች እያስወገዱ እያለ የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ ...